ጥልቅ አተነፋፈስ የሚያስተምረን
የታተመበት ቀን የተሻሻለበት ቀን
ጠዋት በነቁበት ቅጽበት፣ ገና ተኝተው ሳሉ፣
በቀስታ፣ በልብዎ ውስጥ፣
የቅዱሱን «ቃል» እየተናገሩ፣
በተሰበሰቡ ከንፈሮች በኃይል ትንፋሽ ያውጡ፣
የቻሉትን ያህል ረጅም
ያውጡ፣ ያውጡ፣ ሙሉ በሙሉ ያውጡ፣
አሁንም ማውጣትዎን ይቀጥሉ
«ከዚህ በላይ አይወጣም» ብለው ሲያስቡ፣
የትንፋሽዎን የመጨረሻ ቅሪት ጨምቀው ያውጡ
ያን ጊዜ፣
ውሃ ወደ ለስላሳ ጥጥ እንደሚሰርግ፣
ኦክስጅን ወደ ሳንባዎችዎ ይፈስሳል
ከዚያም ተነሥተው ይቀመጡ፣
ተንበርክከው ወይም ወንበር ላይ ተቀምጠው፣
ሂደቱን ይድገሙ
ከዚያም ቆመው እንደገና እንዲሁ ያድርጉ
ብዙ ጊዜ ሲደግሙት፣
20 ሰከንድ፣ 30 ሰከንድ፣ 1 ደቂቃ፣ አንድ ደቂቃ ተኩል፣
የሚያስገቡት አየር ይጨምራል፣
ይበልጥና ይበልጥም፣
የሚያወጡት አየር ይጨምራል
በመጨረሻ የሚያወጡት ትንፋሽ በእውነት ሳይቀር ሲቀር፣
ውሃ ወደ ጉድጓድ እንደሚጣደፍ፣
ኦክስጅን በአንድ ጊዜ ወደ ሳንባዎችዎ ይጎርፋል፣
ትኩስ የሕይወት ንጥረ ነገሮች መላ ሰውነትዎን ሲሞሉ ይሰማዎታል
ቀንዎን በዚህ መንገድ ይጀምሩ፣
በተሞላ ልብና አካልም
ብሩህ ቀን ማሳለፍ ይችላሉ
ነቅተው ሳሉ ብዙ ጊዜ
ይህን «ሙሉ በሙሉ ትንፋሽ ማውጣት» ቢያደርጉ፣
የመታደስ ኃይል በልብና በአካል ውስጥ ይነሣል፣
ቅዱስ ንቃተ ህሊናም በቀላሉ ይዘልቃል

በአተነፋፈስ ከሰዎች ጋር ተገናኝተናል፣
ከአየርና ከውሃ፣ ከምድርም ጋር ተገናኝተናል፣
ከዕፅዋትና ከእንስሳት ጋር ተገናኝተናል
አይደለም፣ ከዚያም በላይ፦
ከከዋክብትና ከጽንፈ ዓለም ጋር ያለን ግንኙነት እንኳ
የሚፈጸመው በጥልቅ አተነፋፈስ ነው
የተረጋጋው የዕለት ተዕለት አተነፋፈሳችን
የአንድነትን ልብ ራሱን ሲያስተምረን ነበር
አንድም ቃል ሳይናገር

